የአድአው ጥቁር አፈር (ዝክረ ተስፋዬ ገብረአብ) ክፍል ፫
Arts

የአድአው ጥቁር አፈር (ዝክረ ተስፋዬ ገብረአብ) ክፍል ፫

ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ ተስፋዬ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ኃላፊ ሆኖ በመሾሙ አልተደሰተም። “ከችሎታዬ በላይ እና ከፍላጎቴ ውጪ ነው የተሾምኩት” እያለ ለኃላፊዎቹ ይናገር ነበር። እያደር ደግሞ መሥሪያ ቤቱ የጭቅጭቅና የአምባጓሮ መድረክ ሆኖ አገኘው። የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ የነበረው በረከት ስምኦን እና የደህንነት መሥሪያ ቤቱ በፕሬስ ድርጅት ስር በሚታተሙት ጋዜጦች ላይ ለሚወጡ እንከኖች የተለያዩ ትርጉሞችን እየሰጡ ያጨናንቁት … Continue reading

የአድአው ጥቁር አፈር (ዝክረ ተስፋዬ ገብረአብ) ክፍል ፪
Arts

የአድአው ጥቁር አፈር (ዝክረ ተስፋዬ ገብረአብ) ክፍል ፪

“የሄድኩበት ፍጥነት “ሰኞ ተወለድኩ፣ ማክሰኞ ተረገዝኩ፣ ዕሮብ ክርስትና ተነሳሁ፣ ሐሙስ እንጨት ለቀማ ሄድኩ” የሚለውን የስንዝንሮን ታሪክ የሚያስታውስ ነበር” የተስፋዬ የዚህ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሆኖ መሾም ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ ከመሾሙ አራት ዓመት ቀደም ብሎ (በ1979) በዚህ መሥሪያ ቤት የጋዜጣ ሪፖርተርነት ቦታ እንዲሰጠው በማመልከቻ ጠይቆ በመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ምላሽ ተነፍጎት የነበረ መሆኑ ነው። የያኔው የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ታዋቂው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ነበር። ደርግ እስኪወድቅ ድረስ መሥሪያ ቤቱን የመራው እርሱ ብቻ ነው። እርሱ ከስልጣኑ ተነስቶ ነው ተስፋዬ ገብረአብ በቦታው የተሾመው።
Continue reading

የአድአው ጥቁር አፈር (ዝክረ ተስፋዬ ገብረአብ) ክፍል ፩
Arts

የአድአው ጥቁር አፈር (ዝክረ ተስፋዬ ገብረአብ) ክፍል ፩

ምክትል የመቶ አለቃ ተስፋዬ ገብረአብ እና ሃያ የሚሆኑት ጓዶቹ የተመደቡት በጎንደር ክፍለ ሀገር፣ ጋይንት አውራጃ የነበረውን የ603ኛ ኮር እንቅስቃሴ እንዲዘግቡ እና የፕሮፓጋንዳ ጽሑፍ እንዲያዘጋጁ ነበር። ይሁንና የአንድ ወር ደመወዝ እንኳ ሳይቀበሉ በታላቁ የደብረ ታቦር ውጊያ ላይ ከያኔው የኢህአዴግ ሰራዊት ጋር ፍልሚያ ገጠሙ። በውጊያው ከሁለቱም ወገን ብዙዎች አለቁ። የኢትዮጵያ ሠራዊት አዛዦች በሂሊኮፕተርና በጂፕ አመለጡ። ተስፋዬ ገብረአብ ደግሞ የኢህአዴግ ጦር በተኮሰው መትረየስ ግራ እጁ ላይ ክፉኛ ተመትቶ ህሊናውን ሳተና ከአንድ ገደል ስር ገባ። ከነበረበት የሰመመን ዓለም ሲባንን ራሱን የወያኔ ምርኮኛ ሆኖ አገኘው። Continue reading