መለስ ዜናዊን በጨረፍታ
በኢትዮጵያ ታሪክ ለረጅም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ መለስ ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1/1947 ዓ.ም በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ ነው። መለስ የልደት ስማቸው “ለገሠ ዜናዊ” ነበር። ተማሪ ለገሠ ዜናዊ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ እንደነበረ ብዙ የተባለለት ጉዳይ ነው። እስከ ስምንተኛ ክፍል የተማረው በአድዋው ንግሥተ ሳባ ትምህርት ቤት ሲሆን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (Highschool) ትምህርቱን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ሁለተኛ …