Arts

የኤልያስ መልካ ስራዎች

በሮቤል

በመጀመሪያ ይህን ፅሁፍ እንድፅፍ ምክንያት የሆነኝ ነገር ኤልያስ መልካ ብዙ ቃለምልልሶች ላይ ስንት አልበሞች ሰርተሀል ሲባል መቁጠሩ ምን ያደርጋል በግምት 40 ይሆናሉ ይላል እውነታው ግን ኤልያስ ሙዚቃ ማቀናበር በጀመረባቸው የመጀመርያ ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ ብቻ 40 አልበሞችን ሰርቷል፡፡

መንፈሳዊ የመዝሙር አልበሞችን ጨምሮ በአጠቃላይ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ደግሞ ከ60 በላይ አልበሞችን (ከ600 በላይ ስራዎችን) አቀናብሯል ብዙ ነጠላ ዜማዎችን እንዲሁም ከ100 በላይ ግጥምና ዜማዎችን ሰርቷል ይሄ ሁሉ ታድያ የሆነው ከ1991-2012 ዓ.ም. (በ20 ዓመታት ውስጥ) ነው፡፡ ሙዚቀኞቻችን አንድ አልበም ለመስራት የሚፈጅባቸውን ዓመታት ካስተዋልን ኤልያስ ምን ያህል እራሱን ለስራው የሰጠ ልዩ ሠው እንደሆነ ወለል ብሎ ይታየናል፡፡

በእኔ አቅም የሠበሠብኳቸውን ስራዎች እነሆ……እኔ ያልጠቀስኳቸውን ስራዎች ኮሜንት ላይ መፃፍ የእናንተ ይሆናል፡፡

ከ1991-1999 ዓ.ም. የተሰሩ አልበሞች
1. መሀሙድ አህመድ = ሁሉም ይስማ ፡1991
2. ቴዲ አፍሮ = አቦጊዳ ፡ 1993
3. ሀይልዬ ታደሠ = አንቺን ይዞ
4. ትዕግስት በቀለ = ሳቂታው ፡ 1994
5. ትግሪኛ ኮሌክሽን = በፍቅሪ ሸፊተ
6. ምስራቅ ኤፍሬም = ሚስጥሬ
7. ተሾመ ወልዴ = አቻዬ መልሴ
8. ላፎንቴን = ጓደኝነት
9. አሌክስ እና ጎሳዬ = ኢቫንጋዲ : 1994
10. አብነት አጎናፍር = ድብቅ ውበት ፡ 1995
11. ሙሉ ሲሳይ(ሞኒካ) = ሸክሽክ
12.ጌድዮን ዳንኤል = በተራ ፡ 1996
13. ይርዳው ጤናው = ጀንበር፡ 1994
14.
15. ሚካኤል በላይነህ = አንተ ጎዳና: 1996
16. ገረመው አሠፋ = ንፁህ ነሽ
17. ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ = ልዑል አስወደደኝ፡ 1997
18. ሀይልዬ ታደሰ = ሁሌ ሀሌ
19. አስቴር ግርማ = እሺ ግድየለም፡ 1997
20. ቴዲ አፍሮ = ያስተሰርያል፡ /ከግማሽ በላይ፡ 1997
21. አረጋኸኝ ወራሽ = በቃ በቃ
22. ኩኩ ሰብስቤ = ጊዜ ስጠኝ፡ 1994
23. ጥበቡ ወርቅዬ = አላማርርም /በከፊል/
24. ምንውየለት አባተ = ጀመረኝ፡ 1995
25. ጎሳዬ ተስፋዬ = ሳታመሀኝ ብላ/በከፊል/1998
26. ምናሉሽ ረታ = ባልሳሳት ብያለሁ
27. ኤልያስ የማነ ኪዊ = ይበቃል
28. እንዳለ አድምቄ = ኦሮማይ
29. ዘመነ መለሠ = አልወለድም
30. ዳዊት መለሠ = አይፍቀውም / በከፊል /
31. ማዲንጎ አፍዎርቅ = አይደረግም፡ 1997
32. ግርማ ገመቹ = ትመቺኛለሽ
33. ጌቴ አንለይ = ቼ በል ልቤ፡ 1997
34. ሀብ እንግዳው = በላይ በላይ ያውላት፡1998
35. ደረጄ ዱባለ = አይኔን አላሽም፡ 1998
36. ናትናኤል ሀይሌ = ሌት ይነጋል
37. አብነት አጎናፍር= ውለታ/ከግማሽ በላይ/ ….1999
38. ሚካያ በሀይሉ = ሸማመተው፡ 1999

ከ2000ዓ.ም. እስከ ህይወቱ ፍፃሜ
39. ዘሪቱ ከበደ = እንዳይገለኝ፡ 2000
40. እዮብ መኮንን = እንደ ቃል፡ 2000
41. ሄኖክ አበበ = ቀና እንበል፡ 2000
42. ታምራት ደስታ = አይከብድም ዎይ/በከፊል /:2000
43. አረጋኸኝ ወራሽ = ቻይበት፡ 2001
42. ሐይሌ ሩት = ቺጌ፡ 2003
43. አቤል ሙሉጌታ = ተገርሜ ፡2003 /በከፊል/
44. ሀይልዬ ታደሰ = ፍቅር፡ 2004
45. ግርማ ተፈራ ካሳ = እኔ አይደለሁማ፡ 2006
46. ዳን፡አድማሱ=ዘበናይ፡ 2007
47. ጌቴ አንለይ=መልክሽ አይበለጥሽም፡ 2008
48. ቤሪ = ከምን ነፃ ልውጣ
49. ዘለቀ ገሠሠ = አይዞን /በከፊል/: 2011
50. ልዑል ሀይሉ = እሳቱ ሠዐት፡ 2011

መንፈሳዊ የመዝሙር አልበሞች
1. አገኘሁ ይደጉ
2.ተከስተ ጌትነት፡ 1994
2. ሶፍያ ሽባባው፡ 1997
3. ሰለሞን ይርጋ
4. እንዳለ ወ/ጊዮረጊስ
5. ቤተልሔም ወልዴ
6. ከፅዮን ባንድ ጋር በመሳሪያ የተቀናበረ አልበም
እንዲሁም በመረጃ እጥረት ያልተጠቀሱ ሌሎችም…

ነጠላ ዜማዎች
1. ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ=ስኳርን አየሗት
2. ኪዳኔ ሀይለ= ኩናሚኛ
3. አስቴር ግርማ= ኖርኩ እስካሁን
4. አለማየሁ እሸቴ= የፍቅር ቃል
5. ጌቴ አንለይ = ፎሌ (ኦሮሚኛ)
6. ዘሩባቤል ሞላ= ግልፁን ስሚኝ (አልበሙ ላይ የተካተተ)

ትምህርት ሰጭ ማህበረሰባዊ ስራዎቹ
1.ማለባበስ ይቅር (አብዱ ኪያር፣ሚካኤል፣ጎሳዬ፣ፀደኒያ እና ሌሎችም)*
2. መላ መላ መላ (አለማየሁ እሸቴ፣ ዘሪቱ፣ እዮብ፣ ምኒሊክ ወስናቸው እና ሌሎች)
3.አዲስ አስተሳሰብ (ሀይልዬ ታደሰ፣ ብርሀኑ ፣ታደለ ሮባ እና ሌሎችም)
4. መታመን ማመን (ፀደኒያ፣ታደለ ሮባ እና ሌሎችም)
5. እንኑር ለሌላው (ግርማ እና ሀይልዬ)
6. የላቡን ሲቀማ (ቴዲ አፍሮ፣ ሀይልዬ ታደሰ እና ሌሎችም)
7. ማሊ ሀራ /ኦሮሚኛ (አሊ ቢራ፣ታደለ ገመቹ፣ ሞገስ ተካ እና ሌሎችም)
8. አሽከርክር ረጋ ብለህ (ጎሳዬ፣ ግርማ ተፈራ፣ ምናሉሽ ረታ እና ሞገስ ተካ)
9. መኖርህን ሌሎች ይሻሉ (ጆኒ ራጋ፣  ዘሪቱ እና አብነት)
10. ምሩን (ሀይሌ ሩት፣ ጌቴ አንለይ እና ዘለቀ ገሠሠ)
11. ፋና (ቤቲ ጂ፣ ዘሪቱ፣ ሞገስ ተካ፣ ሀይሌ ሩት እና ሌሎችም

Leave a comment