Features/ Reviews

“የኢትዮጵያ ህዳሴ የእርቅና የአንድነት የሽግግር መንግሥት” መቋቋም አስፈላጊነት

(ለኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤትና ለመገናኛ ብዙኀን ለውይይት የቀረበ መነሻ ሐሳብ)
(ልደቱ አያሌው፤ መጋቢት፥ 2012 ዓ.ም.)

ከዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን መምጣት ጋር ተያይዞ በሀገራችን የተከሰተውና ከፍተኛ የሕዝብ ተስፋ ፈጥሮ የነበረው የለውጥ ሒደት ወደ መክሸፍ አቅጣጫ እየሄደ ነው። ለውጡ ሁሉን አቀፍ በሆነየሽግግር ተቋምና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር በመነጨ ፍኖተ ካርታ መመራት ሲገባው፣ በተጨማሪም ሀገር አቀፍ ብሔራዊ እርቀ ሰላም በማካሄድና መሠረታዊ የፖለቲካ ቅራኔዎቻችንን በተገቢ የሕግና የመዋቅር ማሻሻያዎች መፍታት በሚያስችል አግባብ መካሄድ ሲገባው፣ ከዚህ በተቃራኒ ገዢው ፓርቲ “እኔው አሻግራችኋለሁ” በሚል የተለመደ መታበይ ሒደቱን ብቻውን ሊመራው በመፈለጉ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የለውጥ ሒደት በሚያሳዝንሁኔታ የመክሸፍ አደጋ ገጥሞታል።

ሥልጣን ሲይዝ የሽግግር ሒደቱን በአግባቡ መርቶ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ቃል የገባው “የለውጥ አመራር” ሕዝብ የሰጠውን አደራ በአግባቡ ከመወጣት ይልቅ ሳይውል ሳያድር ወደ ሥልጣን ሽኩቻ ውስጥ በመግባት ያለፈው የሃያ ሰባት ዓመት ሥርዓት ተቀጽላ እንጂ እውነተኛ የለውጥ ኀይል አለመሆኑን በተግባር አሳይቷል። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መለስተኛ ከሚባሉ ጥገናዊ ለውጦች ባለፈ ሀገሪቱ ትርጉም ባለው የተሐድሶ ወይም የሽግግር ሒደት ውስጥ እንዳልሆነች ግልጽ እየሆነ መጥቷል። የለውጥ አመራሩ የወቅቱን ሒደት ወደ በጎ አቅጣጫ ማሸጋገር ይቅርና ሀገሪቱን “ከድጡ ወደ ማጡ” በሚያስብል ደረጃ ወደ ባሰ አደጋ እየመራት ይገኛል። ይህ የለውጥ ሒደት ወደ ስኬት ሳይሆን ወደ ክሽፈት እየተቃረበ መሆኑ በግልጽ እየታየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከፊታችን ሊካሄድ የታሰበው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ችግሮቻችንን ከመፍታት ይልቅ ወደ ባሰ ሀገራዊ ቀውስ ሊያስገባን ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት በበርካታ ዜጎች ዘንድ ፈጥሯል። በእኛ እምነት፥ ይህ ስጋት ከተጨባጭ ምክንያት የመነጨ ተገቢ ስጋት ነው። ስኬታማ ሽግግር ባላካሄድንበት ሁኔታ ወደ ሀገራዊ ምርጫ ለመግባት መሞከር ወደ ቅድመ 2010 ዓ.ም. ሁኔታ እንድንመለስ፣ ወይም ወደ ባሰ የሀገርን ህልውና የሚፈታተን የፖለቲካ ቀውስ እንድንገባ ከማድረግ ባለፈ ወደ ዘላቂ መዋቅራዊ ዴሞክራሲ ሊያሸጋግረን አይችልም።

የወቅቱ ውስብስብ የፖለቲካ ችግራችን፣ በሕዝብ የተሰጠውን ዳግም ዕድል በአግባቡ መጠቀም ሳይችል በቀረውና አሁን በሥልጣን ላይ በሚገኘው “የለውጥ ኀይልም” ሆነ የከሸፈ ሽግግርን ተከትሎ በሚመጣ የይስሙላ ምርጫ ሊፈታ አይችልም። ከእንግዲህ ችግራችን ሊፈታ የሚችለው በአንድ የሽግግር ሒደት ሊፈጸሙ የሚገባቸውን ሀገራዊ ጉዳዮች በአግባቡ ለመፈጸም የሚችል አንድ ሁሉን አቀፍ የእርቅና የአንድነት የሽግግር መንግሥት በማቋቋም ነው። ነገር ግን “የሽግግር መንግሥት መቋቋም አለበት” የሚል አቋም ስንይዝ በቅድሚያ ለምን የወቅቱ የሀገራችን የፖለቲካ ችግር በመደበኛ የምርጫ ሒደት ሊፈታ እንደማይችል አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ አለብን። ስለሆነም፥ ምን ዓይነት የሽግግር መንግሥት ያስፈልገናል? በማንና እንዴትስ ሊቋቋም ይችላል? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከመሞከራችን በፊት፣ “ወደ ምርጫ መግባት የለብንም” የምንልበትን ምክንያት በቅድሚያ ዘርዘር አድርገን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

Read full document here

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s